በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን አልፏል
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን መብለጡ ተገለፀ፡፡
በሃገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 511 ሺህ 485 የደረሰ ሲሆን ÷8 ሺህ 366 ሰዎችም ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው፡፡
በዚህም ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ግብፅ፣ናይጄሪያ እና ጋና ተከታዩን ደረጃ ይይዛሉ፡፡
በግብፅ 94 ሺህ 483 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 4 ሺህ 865 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በናይጄሪያ ደግሞ 43 ሺህ 841 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን÷ 888 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ነው የተባለው፡፡
እንዲሁም በጋና 37 ሺህ14 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 182 የሚሆኑት ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
እንደ ወርልድ ኦ ሜትር መረጃም በአጠቃላይ በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ1 ሚሊየን የተጠጋ ሲሆን በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 20 ሺህ 350 ደርሷል፡፡
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።