Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ የተመራ ልዑክ የላኒው ፋብሪካን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ እና የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ዑማን ያካተተው ልዑክ በጉራጌ ቡኢ ከተማ አስተዳደር በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የተቋቋመውን የላኒው ፕሌይ ውድ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጎበኙ።
የላኒው ፕሌይ ውድ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ274 ሚሊየን ብር የተቋቋመ ፋብሪካ ሲሆን ችፑድ በማምረት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ፋብሪካው በአሁኑ ሰዓት ለ162 ቋሚ ሰራተኞች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን የቡኢ ከተማ ህዝብን የመብራት እና የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።
በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልዑክ ሌሎች የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.