Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱ ተገለፀ

አዲስ አበበሳ፣ጥር 17፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱን የክልሉ የግብር እና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የበረሃ አንበጣ መንጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ህብረተሀሰቡ የተለያዩ ባህላዊ የመከላከያ ዘዴዎችን በመጠቀም ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ እና ይህም አበራታች ውጤት ማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡

ህብረተሀሰቡ የአንበጣ መንጋው ሊያደርሰው የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያደርገውን ርብርብ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ቢሮው አሳስቧል፡፡

የበረሃ አንበጣው ወላይታ ፣ ጌዴኦን ጨምሮ በስድስት ዞኖች የተከሰተ ሲሆን በሀዋሳ እና በሁለት ልዩ ወረዳዎችም መከሰቱ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.