Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ወጣቶች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ክልል በዘንድሮው የክረምት ወቅት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገለጸ፡፡

በተያዘው የክረምት ወራት በሚካሔደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አስተዋጽኦ ለማበርከት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ወጣቶች ፌደሬሽን አስታውቋል ፡፡

የደቡብ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት ሱልጣን አሊ እንዳስታወቀው ÷በክልሉ የ2014 ዓ.ም የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ወጣቶች በልዩ ልዩ የስራ መስኮች ይሳተፋሉ።

5 ሚሊየን 592 ሺህ 186 የህብረተሰብ ክፍሎችም ተጠቃሚ ይሆናሉ የተባለ ሲሆን ÷ ከመንግስት ይወጣ የነበረውን ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ማዳን እንደሚቻል መገለፁን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣ የአረጋውያን ቤት ግንባታና ጥገና እንዲሁም በሌሎችም መስኮች ስራዎች እንደሚከናወኑ ተገልፆ ለሚካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ መላው የክልሉ ወጣቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በክልሉ ባለፈው አመት በተካሔደው የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ የገለጸው ወጣት ሱልጣን ከዚህ ቀደም የነበረውን የመረዳዳት እና የመደጋገፍ እሴት ይበልጥ እንዲጎለብት በትኩረት ይሰራል ብሏል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.