Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ከ 3 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ መሰማራታቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ከ 3 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ መሰማራታቸው ተገለፀ፡፡

እየተካሄደ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለጹት በዞኑ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በተደረገ ጥረት ከ 3 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች ተሰማርተው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለጻ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች ያሉት የቤንች ሸኮ ዞን በግብርናው ዘርፍ፣ በቡና እና በቅመማቅመም ፣በማር ምርት፣ በቅባት እህሎች፣ በሩዝ እርሻ ልማት ፣በሆርቲካልቸር እና መሰል ገበያ ተኮር በሆኑ ዘርፎች ላይ የባለሀብቱን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም የባለሀብቱን ተሳትፎ ለማሳደግ እና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በትኩረት ይሰራል ሲሉ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.