Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ62 ሺ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት ምክንያታዊ የወጣቶች የውይይትና ክርክር መድረክ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል ወጣቶች ፌደሬሽን ከነገ ጀምሮ በክልሉ በሚገኙ በሁሉም ከተሞች 4ተኛ ዙር ምክንያታዊ የወጣቶች የውይይትና የክርክር መድረኮች እንደሚካሄዱ አስታውቋል።

የደቡብ ክልል ወጣቶች ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ወጣት ሱልጣን አሊ እንዳስታወቀው የዛሬ ሀገር ገምቢና የነገ ሀገር ተረካቢ የሆነው ወጣቱ ትውልድ በሁለንተናዊ መልኩ ብቁ ሆኖ ሀገሪቱን የሚረከብበት ምቹ ሁኔታ ሊፈጠርለት ይገባል።

ፕሬዝዳንቱ በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ የወጣቱ ሚና በሚል ርዕስ ነው የክርክርና የውይይት መድረኩ ገልጸዋል።

በተለይም ደግሞ ወጣቱ ሀይል በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ አወንታዊ ሚና እንዲጫወት፣ ስለ ሀገሩ ያለውን አመለካከት በትክክለኛው መንገድ መቅረፅ እና ብቁ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ።

በዚህም በሁሉም ጉዳይ ላይ ምክንያታዊነትን ተላብሶ ህይወቱን ሊመራ፣ ሀገሩን ተረክቦ ሃላፊነት ሊያስተዳድር ይገባል ያለው ወጣት ሱልጣን በየጊዜው በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቂ መረጃ ይዞ በእውቀት የሚመራ፣በምክንያት የሚያምን ሊሆን እንደሚገባም ጠቁሟል።

በሀገራችነን እየተካሄደ ባለው የለውጥ ሂደት የወጣቱ ሚና ከፍተኛ እንደነበረ የሚታወቅ ቢሆንም በሌላ በኩል በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የፀረ ለውጥ ሀይሉን እኩይ ተግባር አራማጅ የሆኑ ወጣቶች የሚታዩ በመሆኑ ይህን አጥፊ መንገድ ለመቀልበስ ሁሉም ወጣት ሃላፊነት አለበትም ነው ያለው።

በክልሉ የዚህ አይነት የውይይትና የክርክር መድረኮች ወጣቱ ምክንያታዊነትን እንዲላበስ የሚያግዙ እንደሆኑም ወጣት ሱልጣን አስታውቋል ።

በክልሉ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ጥር 14 እና 15 እንዲሁም በሁሉም የወረዳ ከተሞች ከጥር 22 ጀምሮ መድረኮቹ ይካሄዳሉ።

በእነዚህ መድረኮች ከ62 ሺ በላይ ወጣቶች የክልሉ ወጣቶች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.