Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል የበረሃ አንበጣ መንጋ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በደቡብ በክልል በተለያዩ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ መከሰቱ ተገለጸ፡፡

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንደገለጸው፣ ሁለት የአንበጣ መንጋ በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመርና በናጸማይ ወረዳዎች፣ሁለት መንጋ ደግሞ በአሌ ልዩ ወረዳ ተከስቷል።

የአንበጣ መንጋው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ከሁለት ሳምንት በፊት መከሰቱን ጠቅሰው÷ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ወደ ደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ እና አሌ ልዩ ወረዳ እንደተሸጋገረ ነው የተገለጸው፡፡

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው በመከላከል ስራው በሐመርና በናጸማይ ወረዳዎች ተከስቶ የነበረውን መንጋ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ነው የጠቀሱት፡፡

በአሌ ልዩ ወረዳ ውስጥ የተከሰተውን ሁለት የበረሃ አንበጣ የመከላከል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የበረሃ አንበጣ መንጋ በአጭር ጊዜ ብዙ ርቀት በንፋስ ሃይል የመጓዝ አቅም ስላለው በአጎራባች አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የአሰሳ ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም መልእክት ተላልፏል።

ህብረተሰቡ የአንበጣ መንጋን አስመልክቶ ተዛማጅነት ያለው አዲስ ነገር ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የግብርና ቢሮዎች ማሳወቅ እንደሚገባም ተገልጿል።

 

በአወል አበራ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.