Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኮሪያ ኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መነሻውን ቻይና ያደረገው የኮሮና ቫይረስ ወደ ደቡብ ኮሪያ መዛመቱ ተነግሯል።

በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም ነው የተገለፀው።

በደቡብ ኮሪያ በኮሮና ቫይረስ  አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ቀን ብቻ በእጥፍ መጨመሩ ነው የተገለፀው።

ከሀገሪቱ የወጣው መረጃም በትናነትናው እለት ብቻ 229 አዲስ ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ነው የተገለፀው።

ይህም አጠቃላይ  በሀገሪቱ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 433 አድርሶታል።

ሁለት ታማማሚዎችም በበሽታው ለህልፈት መዳረጋቸውን የተገለፀ ሲሆን፥ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት አለ ነው የተባለው።

ባለስልጣናት እንዳረጋገጡትም በበሽታው አዲስ ከተያዙት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአገሪቱ ደቡብ ምሥራቅ በምትገኘው የዴጉ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆስፒታልና የሐይማኖት ስፍራ ጋር የተያያዙ ናቸው።

የሀገሪቱ ምክትል የጤና ሚኒስትር በሽታው አሳሳቢ የሆነ አዲስ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።

ደቡብ ኮሪያ ከቻይና ውጪ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር የሚበዙባት ሀገር ሆናለች።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.