Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ወሎ ዞን ከ350 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች ድጋፍ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ለሚገኙ ከ350 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች ድጋፍ እያደረኩ ነው አለ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት።

የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ መሳይ ማሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንደተናገሩት ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተፈናቃይ የማህበረሰብ ክፍሎችን መንግስት በትኩረት እየደገፈ ነው።

በ22 ትምህርት ቤቶች ተጠልለው ለሚገኙና ማህበረሰቡ ውስጥ ላሉ ተፈናቃዮች እሰከ አሁን ከ36 ሺህ በላይ ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል ።

ተፈናቃዮቹ የተጠለሉበት ቦታ የመብራት፣ የውሃና የመሳሰሉት መሠረታዊ ፍላጓቶች እየተሟሉ እንደሆነም ነው የተናገሩት።

ወደፊትም ዘይት፣ ጥራጥሬ እና ሌሎች የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለማሟላት እየተሠራ ነው ያሉት አቶ መሳይ፣ ማህበረሰቡና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ ሌላ መጠለያ ጣቢያ ለማስገባትም እየሰራ ነው ብለዋል።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.