Fana: At a Speed of Life!

በደብረ ብርሃን መስኖ ግድብ ውስጥ ለመዋኘት የገቡ ሶስት ታዳጊዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ መስኖ ግድብ ውስጥ ለመዋኘት የገቡ ሦስት ታዳጊ ህፃናት ሕይወት ማለፉን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

በከተማው የአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ምንውየለት ጭንቅሎ እንደገለጹት፥ ታዳጊዎቹ አሳስ ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኝ ግድብ ውስጥ ለመዋኘት ገብተው ህይወታቸው አልፏል።

በወቅቱ ታዳጊዎቹ ከጥምቀት በዓል መልስ በግድቡ ለመዋኘት በገቡበት ወቅት ለህልፈት መዳረጋቸውንም ተናግረዋል።

የጓደኞቹን መስመጥ የተመለከተው ጓደኛቸው ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሠረት የሁለቱ ታዳጊ አስከሬን ትናንት አመሻሽ ላይ መገኘቱን እና የአንደኛውን ታዳጊ አስክሬን ፍለጋ መቀጠሉንም ኢንስፔክተር ምንውየለት ገልጸዋል።

ሟቾቹ የሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች እንደነበሩም ተመልክቷል።

የሟቾቹ አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው እንዲደርስ ተደርጎ በዛሬው ዕለት ሥርዓተ ቀብራቸው እንደተፈጸመ መናገራቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.