Fana: At a Speed of Life!

በደወሌ ኮሪደር በሚገኝ ኬላ ከጅቡቲ ለሚገቡ አሽከርካሪዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ ለመመርመር የሚያስችል ናሙና መውሰድ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዛሬው እለት በደወሌ ኮሪደር በሚገኝ ኬላ ከጅቡቲ ለሚገቡ አሽከርካሪዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ ለመመርመር የሚያስችል ናሙና መውሰድ ተጀመረ፡፡

ናሙናውን ለመውሰድ የሚያስችልና ለማቆያ የሚያገለግል የድንኳን አልጋ በማዘጋጀት ስራው መጀመሩም ተገልጿል።

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የዲሜሬጅ ህግና ሎጅስቲክ ድጋፍ ዳይሬክተርና የደወሌ የኮሮና መከላከል ግብረሀይል አስተባባሪ አቶ አበበ እሸቱ እንደተናገሩት የተጀመረው ናሙና የመውሰድ ስራ ከጅቡቲ የተለያዩ እቃ ጭነው የሚገቡ አሽከርካሪዎችን ናሙና ወስዶ ልየታ በማድረግ ቫይረሱ የተገኘባቸው ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።

የናሙና ምርመራው ኮንቴኔር የሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ ነው የተጀመረውው፡፡

በታሪክ አዱኛ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.