Fana: At a Speed of Life!

በዱከም በቀን 450 ቶን ብረት ማቅለጥ የሚችል የብረታ ብረት ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ እየተመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ)  በቀን 450 ቶን ብረት የማቅለጥና 600 ቶን ፌሮ ብረት የማምረት አቅም ያለው ታዳሽ የብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካ በዱከም ተገንብቶ እየተመረቀ ዛሬ እየተመረቀ ይገኛል።

50 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ፋብሪካው በ5 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወጪ መገንባቱ ነው የተገለፀው።

ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ  ወደ ስራ ሲገባ ለ700 ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

የውጭ  ምንዛሬን በማስቀረት ረገድም ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።

 

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.