Fana: At a Speed of Life!

በዳሬ ሰላም እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 እና ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ ዳሬሰላም እየተካሄደ ባለው የምሥራቅ አፍሪካ ከ20 እና ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አድርገዋል፡፡

በተካሄዱ የመክፈቻ ውድድሮችም÷ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዘጠኝ ወርቅ፣ አንድ  ብር እና አንድ የነሃስ ሜደዳሊያዎችን ሰብስበዋል፡፡

በአጠቃላይ 11 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ውድድሩን በድል መጀመራቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን  መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.