Fana: At a Speed of Life!

“ከሃገር ልማት እስከ እናት ልማት”- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የፋብሪካው መገንባት በዳቦ አቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም በኑሮ ውድነት እየተጎዳ ላለው የከተማዋ ማህበረሰብ ታላቅ የምስራች ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ዛሬ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በ217 ሚሊየን ብር ወጪ በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባውን ዘመናዊ የዳቦ ፋብሪካ መርቀን ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸውን ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

የፋብሪካውን ቁልፍ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እጅ መረከባቸውንም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

የፋብሪካው መገንባት በዳቦ አቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም በኑሮ ውድነት እየተጎዳ ላለው የከተማዋ ማህበረሰብ ታላቅ የምስራች ነውም ብለዋል።

በ6 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባው የዳቦ ፋብሪካው በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ በማምረት አቅም ያለው ሲሆን÷ ለ450 ዜጎች በተለይ ለእናቶች የስራ እድል ይፈጥራል።

በመሆኑም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ጽህፈት ቤታቸውን በከተማው ነዋሪ ስም አመስግነዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.