Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ቫይረስ ዳግም ተቀሰቀሰ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ቫይረስ ዳግም መቀስቀሱ ተሰማ።

የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ኢቴኒ ሎንጎንዶ በቫይረሱ ሳቢያ ምባንዳካ በተሰኘችው ከተማ አራት ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

ከተማዋ አሁን ላይ በሃገሪቱ ወረርሽኙ ካለበት ስፍራ በ1 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች ነው የተባለው።

ሃገሪቱ ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ ሁለተኛውን የኢቦላ ወረርሽኝ ስርጭት መግታቷን ብትገልጽም ዳግም የኢቦላ ተጠቂዎች ተገኝተዋል።

ከፈረንጆቹ ነሐሴ 2018 ጀምሮ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች በኢቦላ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል።

አሁን ላይ ወረርሽኙ ዳግም በተቀሰቀሰባት ምባንዳካ ከተማ ኢቦላ በፈረንጆቹ 2018 ለመጨረሻ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን፥ በወቅቱም 33 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገው ነበር።

የኢቦላ ዳግም መቀስቀስ በሃገሪቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተዳምሮ ስጋት ደቅኗል።

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.