Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 1 ሺህ 300 ንጹሃን ተገድለዋል – ተመድ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 1 ሺህ 300 ንጹሃን መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

ድርጅቱ በተወሰኑ ወራት ውስጥ በሃገሪቱ ሶስት የተለያዩ ግዛቶች በተቀሰቀሰ ግጭት ሳቢያ የጅምላ ግድያ መፈጸሙን አስታውቋል።

ከዚህ ባለፈም ከግማሽ ሚሊየን በላይ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ነው ያለው ድርጅቱ።

ከግድያዎቹ አብዛኛዎቹ በቅርብ ሳምንታት ኢቱሪ፣ ሰሜን እና ደቡብ ኪቩ የተፈጸሙ መሆናቸውንም ገልጿል።

ለደረሰው አብዛኛው ጥቃትም በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖችን ጨምሮ የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ሃላፊነት ይወስዳሉም ነው ያለው።

የተመድ የሰብአዊ መብት ሃላፊ ሚሼል ባችሌት የተወሰኑት የጅምላ ግድያዎችና ጥቃቶች በወንጀለኝነት እና ሰብአዊ መብት እንደሚያስጠይቁ አስጠንቀቀዋል።

አሁን ላይ እየተባባሰ የመጣውን ጥቃት ተከትሎ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ነው የተባለው።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.