Fana: At a Speed of Life!

በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ እጩዎች የሚኖራቸው ቅደም ተከተል በሎተሪ ዕጣ ይወሰናል- ቦርዱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ እጩዎች የሚኖራቸው ቅደም ተከተል በሎተሪ ዕጣ እንደሚወሰን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ።

ይህም የድምጽ አሰጣጥ ሂደትን ግልጽነት እና ፍትሐዊነት ለመጨመር እንደሚያስችል ታምኖበታል።

ሂደቱ ሁለት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው በእጅ ( ማንዋል ) ሲሆን ሁለተኛው ሂደት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሲስተም የሚከናወን ነው ተብሏል።

በመጀመሪያው ደረጃ የዕጩዎች ስም፣ የፓርቲ ስም እና ቁጥር ያለበት ዝርዝር ፖስታ የያዙ የዕጣ ማውጫ ሳጥኖች ይዘጋጃሉም ነው የተባለው ።

ለተወካዮች ምክር ቤት እያንዳንዱ ዕጩ በተናጥል የሚታይ ሲሆን ለክልል ምክር ቤቶች የግል ዕጩዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች  እንደ አንድ ብሎክ እንደሚታዩ ተነግሯል።

በብሎክ ውስጥ ያሉ ዕጩዎች በተዘበራረቀ መንገድ እንደሚቀመጡ ቦርዱ  ገልጿል ።

የማንዋል ሂደቱ ውጤት አውቶማቲክ ወደ ሆነ የድምፅ መስጫ ወረቀት ማዘጋጃ ስርዓት ይገባልም ነው የተባለው።

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.