Fana: At a Speed of Life!

በድጎማ የሚቀርቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በድጎማ የሚቀርቡ መሰረታዊ የምግብ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ዘይት፣ ስኳርና ስንዴ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ እየገባ በመንግስት ድጎማ ለህብረተሰቡ እየቀረበ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም ስንዴ በወር 655 ሺህ ኩንታል፣ የምግብ ዘይት 40 ሚሊየን ሊትር እንዲሁም 25 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስኳር ወደ ሃገር ውስጥ እየገባ ሲሰራጭ መቆየቱን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የጥራት ንግድ አሰራር እና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ እሸቴ አስፋው ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት ብቻም 392 ሚሊየን ሊትር ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የተናገሩት አቶ እሸቴ እንደ ሀገር እየተስተዋለ ያለውን የመሰረታዊ የምግብ ሸቀጥ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.