Fana: At a Speed of Life!

በጃን ሜዳ ጥምቀተ ባህር የክርስትናና የሙስሊም እምነት ተከታዮች በጋራ የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃን ሜዳ ጥምቀተ ባህር የክርስትናና የሙስሊም እምነት ተከታዮች በጋራ የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ፡፡

የጥምቀት በዓልን ውብና ማራኪ እናድርግ፣ ታቦት ማደሪያ ቦታዎችንም እናጽዳ በሚል መሪ-ቃል ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች በገኙበት በጃን ሜዳ የጽዳት ዘመቻው ተከናውኗል፡፡

የከተራ እና የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በተካሄደው ዘመቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ፍቅር ያሸንፋል ማህበር አባላትና ደጋፊዎች፣ የአካባቢው ነዋሪ ነዋሪዎች እና የጽዳት ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

ተሳታፊዎችም ዘመቻው የክርስትናና የሙስሊም እምነት ተከታዮች አንድነታቸውን እና አብሮነታቸውን ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚን እንደሚፈጥርላቸው መናገራቸውን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.