Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ በ12 ሚሊየን ብር የተገነባው የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ከተማን የመጠጥ ውሃ ችግር መፍታት የሚያስችል በ12 ሚሊየን ብር የተገነባው የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ፡፡
የጅማ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ ኢንተርፕራይዝ የከተማውን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት የሚያስችል ክፍል ሁለት የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታን በማጠናቀቅ ነው ለአገልግሎት ያበቃው፡፡
የኢንተር ፕራይዙ ስራ አስኪያጅ አቶ ጀበል አባፊጣ አዲስ የተመረቀው የውሃ ፕሮጀክት የከተማውን የውሃ ሽፋን ከ79 በመቶ ወደ 93 ነጥብ 8 በመቶ ያሳድጋል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ 13 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ የሚያቀርብ ሲሆን በፊት የነበረው አቅርቦት ላይ ሲጨመር የከተማው የውሀ አቅርቦት በቀን 32 ሺህ ሜትር ኪዩብ እንዲሆን ያስችላል፡፡
በሁሴን ከማል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.