Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን ለ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ለ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ ምርጫ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በዞኑ 1 ሚሊየን 558 ሺህ 304 ሰዎች የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን የዞኑ ምርጫ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሸሪፍ አባ ገላን ተናግረዋል።
በጅማ ዞንና ከተማ 18 የምርጫ ክልልና 1 ሺህ 583 የምርጫ ጣቢያ መኖሩን የገለፁት አቶ ሸሪፍ የ ዘጠኝ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ መድረሱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ወደ ወረዳዎች እየተሰራጨ መሆኑን ተናግረው የቀሪው እየተጓጓዘ እንደሆነ ተናግረዋል።
በጅማ ከተማም በ89 የምርጫ ጣቢያ 113ሺህ 120 መራጮች ድምፅ ለመስጠት የመራጭነት ካርድ የወሰዱ ሲሆን ከነገ ጀምሮ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እንደሚጀመር የጅማ ከተማ ምርጫ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ነቢያት አብርሃም ገልፀዋል።
በተመስገን አለባቸው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.