Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት 945 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት በቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት ከ120 በላይ የተለያዩ ፕሮጄክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።

በ2013ዓ.ም በጅማ ዞን 20 ወረዳዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር ታቅደው የነበሩ 123 ፕሮጄክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የዞኑ ምክትል አስተዳደሪና የፕሮጄክት ልማት ሰብሳቢ አቶ ፀጋዬ ኡመታ ተናግረዋል።

ለፕሮጄክቶቹ 945 ሚሊየን ብር ወጪ ሆኗል ያሉት አቶ ፀጋዬ ኡመታ ከመንግስት በጀት በተጨማሪ የጅማ ዞን ህብረተሰብ 245 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብና 593ሚሊየን ብር የሚገመት የጉልበትና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል።

ፕሮጄክቶቹ ከ2 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል ።

በተመስገን አለባቸው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.