Fana: At a Speed of Life!

በጉለሌ እጽዋት ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በጉለሌ እጽዋት ፓርክ ውስጥ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል እና ወደ ሌላ ቦታ ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር መዋሉን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ስፍራው ለከተማዋ ውበትና ድምቀት መሆኑን እና አዲስ አበባን ከጎርፍ ለመከላከል ከሚያገለግሉ ስፍራዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በእሳት ማጥፋት በርካታ የአዲስ አበባና የፌድራል ፖሊስ አመራሮች፣ የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት ፣ የአዲስ አበባ የእሳት እና የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ባልደረቦች ፣ የመንገዶች ባለስልጣን፣ የአካባቢው አስተዳደር እና ህብረተሰቡ  እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል ብለዋል።

ምክትል ከንቲባ እሳቱን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ተሳትፎ ለነበራቸው አካላት በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ለእሳቱ ምክንያት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ምርመራ እየደረገባቸው እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

ቀሪ ስራዎችን በልዩ  ትኩረት  እንደሚከናወነ የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ መረጃዎችን በጊዜው ለህብረተሰቡ እንደሚደርስም አስታውቋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.