Fana: At a Speed of Life!

በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ በፈረጀቴ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የህዝብ ትራንስፖርት አይሱዙ ቅጥቅጥ ከቦቴ ተሳቢ ጋር ተጋጭተው በተፈጠረ አደጋ ነው ጉዳቱ የደረሰው።

በዚህም የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ 13 ሰዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ጉዳት እንደረሰባቸዉም ተገልጿል።

ወደ አዲስ አበባና ወደ ወልቂጤ የሚጓዙ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ ቅጥቅጥ ከተሳቢ ጋር ተጋጭተው አደጋው ደርሷል።

በአደጋዉ ጉዳት የደረሰባቸዉ 8 ሰዎች ለህክምና እርዳታ ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል እንዲሄዱ ተደርጓል።

ሁለቱ ወደ ህክምና ሲወሰዱ መንገድ ላይ ህይወታቸዉ እንዳለፈም ተገልጿል።

አደጋዉ በደረሰበት ቦታ ላይ የሰባት ሰዎች ህይወት ወዲያው እንዳለፈ ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሀላፊ ዶክተር አብድልሰመድ ወርቁ እንዳሉት ወደ ሆስፒታሉ በአደጋዉ ተጎድተው የገቡት ሰዎች ቁጥር 16 ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ አንድ ሰው ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ሁለት ሰዎች በአደጋው እራሳቸውን የሳቱ ሲሆን ቀሪ 13ቱ ደግሞ ከቀላል እስከ መሃከለኛ የሚባል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.