Fana: At a Speed of Life!

በጋሊኮማ አሸባሪው ህወሓት ዓለም አቀፍ ህግን፥ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን በመጣስ ንፁሃንን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ጨፍጭፏል – ጥናት

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በጋሊኮማ አሸባሪው ህወሓት ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድንጋጌዎችን በጣሰ መልኩ በንፁሃን ህፃናት፣ በሴቶችና አዛውንቶች ላይ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች በመጣስ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ማካሄዱን በጥናት ማረጋገጡን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ ፡፡
የሽብር ቡድኑ በክልሉ በዞን 4 ጎሊና ወረዳ ጋሊኮማ ቀበሌ ላይ የፈፀመውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት በተመለከተ የተካሄደው የጥናት ውጤት የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና የአፋር ክልል የቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት ቀርቧል።
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ በጋሊኮማ በሰብዓዊ ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በመሠረተ ልማቶች ላይ የደረሱ ጉዳቶችን ሳይንሳዊ የምርምር ዘዴና ትንታዎችን በመጠቀም ያዘጋጀው መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የፐብሊኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ኡመር አብዱልቃድር ገልፀዋል።
ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ደንጋጌዎችን በጣሰ መልኩ በንፁሃን ህፃናት ፣ በሴቶችና አዛውንቶች ላይ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በከባድ መሳሪያ ጭምር በመታገዝ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን በመጣስ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ማካሄዱን ጥናቱ ያስረዳል ነው የተባለው።
ወራሪው የህወሓት ቡድን በጋሊኮማ በፈፀመው ጥቃት ምክንያት በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን አካላዊ ፣ ሥነ ልቡናዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን በተመለከተም ውይይት ተደርጓል፡፡
በአሊ ሹምባህሪ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.