Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ከተማ ከ140 ሺህ በላይ ሐሰተኛ የብር ኖት ሲያዘዋውር የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋምቤላ ከተማ ከ140 ሺህ በላይ የነባሩ ገንዘብ ሃሰተኛ የብር ኖት ሲያዘዋውር የተገኘ ግለሰብ ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በጋምቤላ ከተማና አካባቢው በርካታ ቁጥር ያለው ሃሰተኛ የብር ኖት መሰራጨቱን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች መኖራቸውን ገልጾ፤ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር ኡማን ኡጋላ ፤ ዛሬ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው በጋምቤላ ንግድ ባንክ ሃሰተኛ ገንዘቡን በአዲሱ የብር ኖት ለመቀየር ሲሞክር ነው ብለዋል።
ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ሃሰተኛ የብር ኖቱን ከየትና እንዴት እንዳገኘው ተጨማሪ የማጠራት ሥራ እየተካሄደበት እንደሚገኝና ለፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ገልጸዋል።
ከስድስት ቀናት በፊት በከተማው አንድ ግለሰብ ከሁለት ሺህ በላይ ሃሰተኛ የብር ኖት ይዞ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኢዜአ ዘግቧል።
ህብረተሰቡ በግብይት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.