Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ከ1ሺህ 119 ኪሎ ግራም በላይ የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጋምቤላ ክልል ባለፉት 11 ወራት ከ1 ሺህ 119 ኪሎ ግራም በላይ የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አኳታ ቻም እንደገለጹት፥ ገቢ የተደረገው የወርቅ ምርት የተገኘው በክልሉ ዲማ፣ ጋምቤላ፣ መንጌሽ እና የአቦቦ ወረዳዎች በባህላዊ ወርቅ አምራቾች የተመረተ ነው።

በበጀት ዓመቱ የተገኘው የወርቅ ምርት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ854 ኪሎ ግራም በላይ ብልጫ እንዳለው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በበጀት ዓመቱ የተሻለ የወርቅ ምርት ሊሰበሰብ የቻለው ኤጀንሲው ከወረዳዎች ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች በመከናወናቸውና አምራቾችን ለመሳብ የወርቅ ዋጋ በመሻሻሉ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የኮንትሮባንድ አዘዋዋሪዎች ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር መጠናከሩም አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.