Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የውስጥና ድንበር ዘለል የፀጥታ ችግሮችን የመከላከሉ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል-አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የውስጥና ድንበር ዘለል የፀጥታ ችግሮችን የመከላከሉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አስታወቁ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በቦንጋ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል እያሰለጠነ ያለውን የልዩ ኃይል ፖሊሶች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጎብኝተዋል።

ርዕሠ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት፥ የክልሉን ሰላም ዘላቂና አስተማማኝ በማድረግ እንደ ሀገር የተጀመረውን የህልውና ዘመቻ ለማሳካት የፀጥታ መዋቅሩን የማጠናከር ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በክልሉ የፀጥታ ኃይሉ የሀገሪቱን ዳር ድንበርና የክልሉን ሰላም በማረጋገጥ ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ እየተወጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ሠልጣኝ የልዩ ሀይል አባላቱም የክልሉን ሰላም በማጠናከር የበኩላቸውን መወጣት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ በበኩላቸው፥ በክልሉ ከመጣው ለውጥ በኋላ በተሰራው መዋቅር የፀጥታ ሀይል ማጠናከር ላይ ትኩረት በመስጠት መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ትልቅ ስራ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ የውስጥና ድንበር ዘለል የፀጥታ ችግሮችን የመከላከል ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተው ፥ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመከላከሉ ረገድ ከሰልጣኞቹ ብዙ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቡን ዊው፥ ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ጋር ሰፊ ድንበር የሚዋሰን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሙርሌ ጎሳ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች በተጨማሪ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና የሰዎች ዝውውር መኖሩን ተናግረዋል።

ክልሉ የውስጥና ድንበር ዘለል የፀጥታ ችግሮችን የመከላከል ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተው ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመከላከሉ ረገድ ከሰልጣኞቹ ብዙ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።

ድንበር ዘለል ወንጀሎችና የውስጥ ፀረ- ሰላም ኃይሎችን ለመከላከል የልዩ ኃይል፣ የመደበኛና የሚሊሻ ጸጥታ መዋቅሮችን በማጠናከር በክልሉ አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ካቢኔ አባላትና ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.