Fana: At a Speed of Life!

በጋሞ ዞን በጎርፍና ጭቃ ናዳ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍና ጭቃ ናዳ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ።

የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንደተናገሩት፥ በጋጮ ባባ ወረዳ ጋፄ ጎሎ ቀበሌ ከማለዳው 1 ሰዓት ገደማ በጣለው ዝናብ ነው አደጋው የደረሰው።

እንደ ኮማንደር ረታ ተክሉ ገለፃ፥ በዚሁ ወረዳ በጊና ቀበሌ ከተራራ አከባቢ በተከሰተ ናዳና ጎርፍ የሁለት አባወራ ቤትና አትክልት ከነ ሙሉ ንብረቱ በናዳው ተሸፍሏል።

አደጋውን ተከትሎም እስካሁን ባለው መረጃ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን፥ የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊጨምር እንደሚችል ከጋሞ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተመሳሳይ በጋሞ ዞን ገረሴ ወረዳ ጋርባንሳ ጋሎ ቀበሌ ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍና ጭቃ ናዳ ሶስት ቤቶች መስጠማቸውንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

ዝናቡ መቀጠሉ እንዲሁም የናዳው ሁኔታም እንዳልቆ የተገለፀ ሲሆን፥ ይህም የአስከሬን ፍለጋውንም አዳጋች እንዳደረገውም ነው።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.