Fana: At a Speed of Life!

በጋሸና ግንባር የወገን ጥምር ሃይል አርቢት፣ ጋሸናና ሌሎች አካባቢዎችን ነፃ አወጣ

አዲስ ፣አበባ ህዳር 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) በ“ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” የወገን ጥምር ሃይል በወሰደው የማጥቃት እርምጃ በጋሸና ግንባር አርቢት፣ ጋሸናና ሌሎች አካባቢዎችን ነፃ አወጣ።
 
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ የሀገር ህልውናን ለመታደግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እየተመራ በሁሉም ግንባሮች ወደ ከፍተኛ የማጥቃት እንቅስቃሴ የገባው “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በአጭር ቀናት ውስጥ አስደናቂ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል፡፡
 
በዚህም ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ በጋሸና ግንባር የአርቢትን፣ የአቀትን እና የጋሻና ከተሞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡
 
በዚህ ግንባርም ጠላት ለበርካታ ወራት የዘረፈውን ሃብት በመጠቀም እና የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስገደድ የገነባውን ኮንክሪት ምሽግ በተቀናጀ እቅድ የአመራር ጥበብ እና ቴክኖሎጂ በመታገዝ በአነስተኛ መስዋዕትነት መስበር ተችሏል ነው ያሉት፡፡
 
ከዚህ ባለፈም በዚህ ግንባር በርካታ የነፍስ ወከፍ፣ የቡድን እና ከባድ መሳሪያዎች በወገን ጦር መማረካቸውን ነው የገለጹት፡፡
 
የወገን ጦር ጋሸናን መቆጣጠሩም ጠላት በላሊባላ፣ በወልዲያ እና ደሴ የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጽዳት መንገዱን የተመቻቸ ያደርገዋል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡
 
በአንፃሩ ጠላት የዘረፋቸውን ንብረቶች እና እራሱን ይዞ ለመውጣት የሚስችለውን እድል ሙሉ በሙሉ ዘግቶበታል ብለዋል፡፡
 
የወገን ጦር ጋሸናንና አካባቢውን ከመቆጣጠር አልፎ በላሊበላ፣ ወልዲያና ወገልጤና አቅጣጫ ወደ ፊት እየገሰገሰ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
 
በሌላ በኩል በወረ ኢሉ ግንባር ጃማ ደጎሎ፣ ወረ ኢሉ፣ ገነቴ ፣ ፊንጮፍቱ እና አቀስታ ከተሞች ከአሸባሪው ቡድን ሙሉ በሙሉ ነጻ መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
 
በተጨማሪም በሸዋ ግንባር መዘዞ፣ ሞላሌ፣ ሸዋሮቢት እና አካባቢው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ከአሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት ነፃ ወጥተዋል፡፡
 
በየግንባሩ የጠላት ኃይል ዘርፎና አውድሞ እንዳይሸሽ የየአካባቢው ማህበረሰብ ተደራጅቶ አካባቢውን በመጠበቅ ንብረቱን እንዲያስቀር፤ ጠላት እንዲማረክ ወይም እጅ እንዲሰጥ በማድረግ እምቢ ካለም አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.