Fana: At a Speed of Life!

በግልገል በለስ ከተማ ከ450 በላይ ጥይቶችን ለሽፍታ ሊያቀብል የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በንግድ መደብሩ ከ450 በላይ የክላሽና የብሬን ተተኳሽ ጥይቶችን አከማችቶ ለሽፍታ ቡድን ሊያቀብል የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ በወርቅና ብር ጌጣጌጥ መደብሩ ተተኳሽ ጥይቶችን በማከማቸት ለታጠቁ ሽፍቶች ለማቀበል ተዘጋጅቶ እያለ ከማህበረሰቡ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የፀጥታ አካላት ትናንት አመሻሽ ላይ በግለሰቡ የንግድ ሱቅ ውስጥ ባደረጉት ፍተሻ 395 የክላሽና 63 የብሬን በድምሩ 458 ጥይቶችን ይዘዋል።

የዞኑ ኮማንድ ፖስት እንደገለጸው፤ ተጠርጣሪውን ግለሰብ ጨምሮ ከወንጀል ድርጊቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሌሎች ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዞኑ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖርና በዜጎች ላይ ግድያ እንዲፈፀም የሽፍቶች ተባባሪ በሚሆኑ አካላት ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረግ በህግ ተጠያቂ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.