Fana: At a Speed of Life!

በግማሽ ዓመቱ የማዕድን ዘርፉ በእጥፍ ያደገ ሲሆን ኢንዱስትሪና ግብርና ዕቅዳቸውን ማሳካታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የማዕድን ዘርፍ ከዕቅድ በላይ 198 በመቶ ሲያስመዘግብ፤ የኢንዱስትሪ  88 በመቶ እና ግብርና  76 በመቶ ዕቅዳቸውን ማሳካታቸውን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን ያለው ከንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ተጠሪ ተቋማት ጋር ባዘጋጀው የ2013 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻፀም ውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በውይይቱ የወጪ ንግድ ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ጀነራል አቶ አሰፋ ሙሉጌታ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የ2013 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የወጪ ንግድ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርቱም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የወጪ ንግድ ገቢ አፈጻፀም ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 90 በመቶ መሳካቱን ጠቅሰው÷ ከ2012 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ18 በመቶ እድገት ማሳየቱን ነው ያብራሩት፡፡

በመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅዳቸውን ጥሩ አፈፃፀም ያስመዘገቡት ምርቶች የቅባት እህሎች 132 በመቶ፣ ጨርቃ ጨርቅ 127 መቶ እና ጫት 106 በመቶ ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡት ደግሞ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች 62 በመቶ፣ የቁም እንስሳት 64 በመቶ፣ ስጋ 66 በመቶ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አቶ አሰፋ ሙሉጌታ ከፍተኛ ገቢን ከሚያስገኙ የግብርና ምርቶች መካከል ነጭ ቦሎቄ እና ሰሊጥ ከ2012 ተመሳሳይ ወቅት አንፃር የተሻለ አፈፃፀም እንዳስመዘገቡ መግለጻቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.