Fana: At a Speed of Life!

በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ግብዓቶች፣ በስንዴ አቅርቦትና ግብይት ዙሪያ  ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኢንድስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ  በተለይም ምርት ወደ ኢንዱስትሪዎች ማይደርሱበትን ምክንያት በመለየት በገበያው ላይ የሚታየውን የፍጆታ እጥረት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሄደ።

የልማት ድርጅቱ ግብዓት ቅራቢውንና ፈላጊውን ለማገናኘት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ የገለጹት፤ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ በዱቄት አቅርቦት ማነስ ምክንያት በተፈጠረ የዋጋ መጨመር ዜጎች ዳቦ ገዝተው መብላት ማይችሉበት ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል።

አምራቾች ጋር ምርት እንዳለ ቢገለጽም ኢንደስትሪዎች ግን በምርት እጥረት ምክንያት በበቂ ሆኔታ እያመረቱ እንዳልሆነ የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ የምክክር መድረኩ ይህን ችግር ለመፍታት ያለመ ነውም ብለዋል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.