Fana: At a Speed of Life!

በግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ላይ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግብፅ ጋዛ ግዛት የአብዱል ፈታህ አል ሲሲ መንግስትን የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ መሆኑ ተነገረ።

መንግስትን በመቃወም ሰልፍ እየተካሄደባቸው በሚገኙ አካባቢዎች ከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር እንዳለ አልጀዚራ ዘግቧል።

በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚዘዋወሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን ይውረዱ የሚሉ መፈክሮችን የሚያሰሙ እና ባነሮችን የያዙ ተቃዋሚዎች አሳይተዋል።

የቀድሞ የመከላከያ ኮንትራክተር መሀመድ አሊ ባለፈው ዓመት የነበረውን ተቃውሞ ለማስታወስ በትናትናው ዕለት ተመሳሳይ ተቃውሞ እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ነው ከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር እየተደረገ የሚገኘው።

በተመሳሳይ የጸጥታ ሀይሎቹ  ከተቃውሞ ጋር ተያይዞ ታዋቂ ፓለቲከኞች እና አክትቪስቶችን ማሰራቸው ተነግሯል።

እንዲሁም ተቃውሞ በበረታባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ የካፌ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲዘጉ መደረጉም ታውቋል።

ባለፈው ዓመት ባልተለመደ ሁኔታ በሺህዎች የሚቆጠሩ ግብፃዊያን ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲለቁ ለመጠየቀ ተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው የሚታወስ ነው።

በወቅቱም የግብፅ መንስት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ከ2 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ማሰሩ መረጃዎች  አመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.