Fana: At a Speed of Life!

በግንቦት ወር 419 ሚሊየን ዶላር ከወጪ ንግድ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በግንቦት ወር 419 ሚሊየን ዶላር ከወጪ ንግድ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ።
የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ÷በግንቦት ወር 404 ሚሊየን ዶላር ለማግኝት ታቅዶ 419 ሚሊየን (103%) ተገኝቷል ብለዋል፡፡
ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ95 ሚሊየን ዶላር (29%)ጭማሬ አሳይቷልም ነው ያሉት ።
በ11 ወራት 3 ነጥብ 69 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቀዶ 3 ኘጥብ 22 በሊየን እንደተገኘ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.