Fana: At a Speed of Life!

በግድቡ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ያለውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያህዳሴ ግድብ ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አስታወቁ።
 
በኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን መካከል ላለፉት 11 ቀናት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የተለያዩ ታዛቢዎችና ኤክስፐርቶች በተገኙበት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁን ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።
 
ትናንት ምሽት ሶሰት ሰዓት አካባቢ ያለውጤት የተጠናቀቀው ድርድርን አስመልክቶ ለአፍሪካ ህብረትና መሪዎች ቢሮ ሪፖርት እንደሚዘጋጀም ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ጠቁመዋል።
 
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ቢሮ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌት እና ውሃ አለቃቀቅ ደንብ ላይ በሀገራችን፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል እየተካሄደ ያለውን ድርድር በበላይነት ሲመለከተው መቆየቱ ይታወሳል።
ኢዜአ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.