Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ለህልውና ዘመቻው 6ሺህ 500ዩኒት ደም ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለህልውና ዘመቻው ከተለያዩ በጎ ፈቃደኛ ደምለጋሾች 6ሺህ 500ዩኒት ደም መሰብሰቡን የጎንደር ከተማ ደም ባንክ ሃላፊ አቶ ደመቀ ጥላሁን ገለጹ፡፡

ከተሰበሰበው ዩኒት ደም ውስጥ 80 በመቶው ከጎንደር ከተማ የተሰበሰበ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊው ÷ ቀሪው ከተለያዩ ወረዳዎች እንደተገኘ አስረድተዋል።

በሩብ ዓመቱ ደም ባንኩ 3ሺህ ዩኒት ደም የመሰብሰብ ዕቅድ የነበረው ቢሆንም አሸባሪው የህወሓት ቡድን የከፈተውን ጦርነት ተከትሎ የደም ለጋሾች ቁጥር በመጨመሩ ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ሃላፊው ገልጸዋል።

ከፍተኛ የፓለቲካ አመራሮችና ሌሎች ሀገር ወዳድ ዜጎች በደም ልገሳው በንቃት እየተሳፉ ነው ያሉት አቶ ደመቀ ÷ ይህም የህልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።

የተቋሙ ሰራተኞች በመደበኛነት ከሚሰሩት ሙያዊ ደም የማሰባሰብ ተግባር በተጨማሪ የወር ደመወዛቸውን የሰጡ ሲሆን ÷ ስንቅ በማዘጋጀትም ለወገን ጦር አጋርነታቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት።

የጎንደር ደም ባንክ በ2013 ዓ.ም 12 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ እደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በምናለ አየነው

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.