Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ ለልዩ ሀይሎች እና ሚሊሻ እንዲሁም ለመከላከያ ሠራዊት የድጋፍ  ሰልፍ  እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በግንባር እየተዋደቁ ላሉ ልዩ ሀይሎች እና ሚሊሻ እንዲሁም ለመከላከያ ሠራዊት የድጋፍ  ሰልፍ  እየተካሄደ ነው።

የአማራ ሕዝብ ልዩ ኀይሉን ለማጠናከርና ደጀን ለመኾን እያደረገ ያለውን ተነሳሽነት ለማበረታታት የአማራ ፖሊስ የማርች ባንድ አባላትም  በጎንደር ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ትርዒት እያሳዩ ነው።

የክልሉን እና የኢትዮጵያን  ሰላም ለመጠበቅ የአማራ ልዩ ኀይል ፖሊስን እንዲቀላቀሉ እና በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ መመከት እንደሚገባም ጥሪ መቅረቡን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ማስታወቁን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.