Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ ከጥምቅት ጋር ተያይዞ ርችት መተኮስ እና ከፀጥታ አካላት ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መዘዋወር የተከለከለ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓል በጎንደር የሚታደሙ ሰዎች ለበዓሉ በሰላም መከበር የበከሉላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጠየቀ።

ከተለያዩ የአለም ሀገራት የመጡ እጅግ በርካታ ጎብኝዎች በሚታደሙበትና በዩኒስኮ ” በማይዳሰስ የሠው ልጆች ባህላዊ ቅርስነት የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

በመሆኑም ለደስታ በሚል ምክንያት ሮኬትም ሆነ ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ እንደሆነ ተገልጿል።

እንዲሁም የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ ከመንግስት የጸጥታ አካል ውጭ በከተማዋ የጦር መሳሪያ ይዞ መዘዋወር የተከለከለ መሆኑን ከከተማ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዩች ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።

ህብረተሰቡ ለእንግዶች የህዝቡን ባህል ፣ ወግ ፣ ትውፊት ፣ ደግነትና በጎ ገፅታዎችን በማስተዋወቅ የበኩሉን ሚና እንዲወጣም ጥሪ አቅርቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.