Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጎንደር ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይትአካሄዱ።
የጎንደር ብልፅግና ፖርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሞላ መልካሙ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት ÷የፌደራል መንግስት የጀመረው ህግ የማስከበር ስራ በህወሓት የጥፋት ቡድን ላይ የሚወሰድ እርምጃ እንጂ ከህዝቡ ጋር ባለመሆኑ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች ከመንግሥት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ውይይቱ በጎንደር ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያለ ምንም ችግር ከወገኖቻቸው ጋር ተረጋግተው እንደሚኖሩ ማሳያና ለችግሮች የጋራ መፍትሔ ለማምጣት ነው ብለዋል።
የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አወቀ አስፈሬ በበኩላቸው÷ በጎንደር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያለ ችግርና ስጋት እንዲንቀሳቀሱ፣ እንዲሰሩና መብታቸውን እንዲያስከብሩ የብልጽግና ፓርቲ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ተወያዮቹ የፌደራል መንግስት በአሁኑ ሰአት በህወሓት ቡድን ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ተገቢና የሚደገፍ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
እንዲሁም የህወሓት የጥፋት ቡድን ከራሱ ጥቅም ባለፈ ለዜጎች ያበረከተው ነገር የለም ያሉ ሲሆን÷ የሀገር ኩራት በሆነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃትም አሳፋሪና የሚወገዝ ነው ብለዋል።
በቀጣይም መንግስት በሚያካሂዳቸው ማንኛውም ጉዳዮች አብሮ በመስራት ለትግራይ ህዝብ ነፃነትና ለኢትዮጵያ ሰላም እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሙሉጌታ ደሴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.