Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ የሚገኙ 5 ክፍለ ከተሞች እየታከሙ ለሚገኙ የሰራዊት አባላት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በጎንደር ከተማ የሚገኙ አምስት ክፍለ ከተሞች በጎንደር ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሚታከሙ የሰራዊት አባላት 28 በጎችን ድጋፍ አደረጉ፡፡

የአምስቱም ክፍለ ከተማ ልዩ ልዩ አደረጃጀት ተወካዮች የድጋፍ በጎችን በሆስፒታሉ እየታከሙ ለሚገኙ የሰራዊት አባላትን እየተንከባከቡ ለሚገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራት አስተባባሪ ወጣት ብርሃኑ አስረክበዋል፡፡

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ እንደገለፁት÷ ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ የወጣት አደረጃጀቶች እያደረጉት ያለውን ድጋፍ ጁንታው መቃብር ወርዶ የህልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

የአዘዞ ፀዳ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ አይናዲስ አበበ÷ ህብረተሰቡ ለሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ጁንታው መቃብር እስኪወርድም ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ ወጣቶች ድጋፋቸን አጠናከረን እንቀጥላን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የዞብል ክፍለ ከተማ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ የሽዋስ ተስፋ÷ በክፍለ ከተማው ህብረተሰቡ ለህልውና ዘመቻው ደጋፍ የሚውል ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የዓይነትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡

ህብረተሰቡ ወራሪው ሃይል እስኪወገድ የደጀንነት ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.