Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር የጥምቀት በዓል ላይ በተኩስ የተቀናጀ ከፍተኛ ፍንዳታ ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበሩ ሁለት የጥፋት ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ዘንድሮ በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ በተኩስ የተቀናጀ ከፍተኛ ፍንዳታ ለመፈፀም የሽብር ተልዕኮ ተቀብለው በዝግጅት ላይ የነበሩ ሁለት የጥፋት ቡድን አባላት ከአራት ኤፍ ዋን ቦምብ እና ከ200 ጥይቶች ጋር በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ክትትል እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣  በአማራ ክልል ፀጥታ ሀይሎች እና በአካባቢው ህብረተሰብ ትብብር በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ የጥፋት ቡድን ያሰማራውን አካል በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ እና የጥፋት ሀይሎቹ ግን አደጋውን ቢያደርሱ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እና መኖሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚሰጣቸው ቃል የተገባላቸው መሆኑን እንዳረጋገጠ አስታውቋል።

የፀጥታ ሀይሎች በቅንጅት ቀን ከለሊት ደከምኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቃቸው በዘንድሮው የጎንደር የጥምቀት በዓል ታዳሚዎች ላይ ሽብር በመፈፀም የንፁሃንን ዜገች ህይወትለመቅጠፍና በንብረት ላይ አደጋ ለማድረስ የታለመውን አደጋ ማክሸፍ መቻሉን ነው የገለፀው።

ዘንድሮ በመላው ሀገሪቱ በሚከበረው የጥምቀት በዓል  ላይ ተመሳሳይ ተልዕኮ ያላቸው አካላት እኩይ ተግባራቸውን ሊፈፅሙ ስሚችሉ ህብረተሰቡ በአካባቢው ከሚገኘው የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት ከበዓሉ ጎን ለጎን ሰላሙንም እንዲጠብቅ አሳስቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.