Fana: At a Speed of Life!

በጠ/ሚ ዐቢይ የሚመራው የወገን ጦር በትናንትናው እለት ያስመዘገበው ድል የሽብር ቡድኑን እንዳፍረከረከው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የወገን ጦር በትናንትናው እለት ያስመዘገበው ድል የሽብር ቡድኑን ህወሃት እንዳፍረከረከው ተገለፀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ አሸባሪ ቡድኑ ህወሃት ከሳምንት በፊት 12 የሚደርሱ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎቹ ተደምስሰውበታል።

ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የሽብር ቡድኑ ወታደሮች መያዛቸውንና በርካቶችም የእጅ ስጡ ጥሪን በመቀበል እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን ነው ያመለከተው።

ቀድሞም ቢሆን በተመሰቃቀለ ሁኔታ ውስጥ የነበረው የሽብር ቡድኑ፥ የትናንቱ የወገን ጦር ድል እንዳፍረከረከው ገልጿል።

በተካሄደው ዘመቻ በጠላት እጅ የነበሩት ዋና ዋና ቦታዎች ማለትም ደሴ፣ ኮምቦልቻ እና ባቲን ጨምሮ ሌሎች አካባቢዎች በወገን ጦር እጅ መሆናቸውን በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መግለጻቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም ሸዋ፣ የከሚሴ ልዩ ዞን እና የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ደቡብ ጎንደርን ጨምሮ አብዛኛው የአማራ ክልል ነጻ መውጣታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡

ተገደንና ተገፍተን በገባንበት ጦርነት በእውር ድንብር የገባው ጠላት በእውር ድንብር እንዳይወጣ ስራ ተሰርቷል የተገኘውም ድል ከፍተኛ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.