Fana: At a Speed of Life!

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ከፍተኛ የአመራሮች ቡድን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታልን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የተመራ ከፍተኛ የአመራሮች ቡድን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታልን ጎበኘ።

በጉብኝቱ ላይ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ፣ ብርጋዴር ጀኔራል ጥጋቡ እና ከፍተኛ የአመራሮች ተሳትፈዋል።

ጉብኝቱ የጎንደር ዩኒሸርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር በተገኙበት የተደረገ ሲሆን፥ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው በአካል በየህሙማን ክፍሉ በመገኘት ታማሚዎችን አነጋግረዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በህግ ማስከበር ሂደት የተጎዱ ጀግኖች የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለሀገራቸው በመዋደቅ ላበረከቱት አኩሪ የጀግንነት ተጋድሎም አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

“ሀገራችሁ ኢትዮጵያ እና ህዝባችሁ የኮራችባችሁ ጀግኖች ናችሁ፤ እዚህ ከፊታችሁ የቆምነው እናንተ ጀግኖች ለሀገራችሁና ለህዝባችሁ ላሳያችሁት የላቀ ጀግንነት በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም ልናመሰግናችሁ ነው፤ ውለታችሁን ሀገራችሁ አትረሳም” ብለዋል።

ልዑካኑ ከጎንደር ሆስፒታል ማህበረሰብና አመራሮች ጋር በመወያየትም ሆስፒታሉ ስለሚጠናከርበት ሁኔታ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.