Fana: At a Speed of Life!

በጤና ተቋማት የሚሰሩ 65 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሚኒስትሯ አስታወቁ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሂደት 49 የጤና ባለሙያዎችና 16 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ባለሙያዎቹ በአብዛኛው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የጤና ተቋማት እየሰሩ የነበሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የጤና ባለሙያዎችና የጤና ተቋማት ሠራተኞች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እያደረጉት ላለው ተጋድሎም ምስጋና አቅርበዋል።

መንግሥት የጤና ተቋማት ሠራተኞችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ከሚያደርገው ሥራ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ራሱን በመጠበቅ የባለሙያዎቹን ጫና እንዲቀንስም ጠይቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለይ ማህበረሰቡ የቫይረሱን ስርጭት የሚመጥን ጥንቃቄ አለመደረጉ እንደሚያሳስባቸው ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

“ጥንቃቄ የምናደርገው የጸጥታ አካላት ወይም የጤና ባለሙያዎችን ትዕዛዝ ለማክበር ሳይሆን፤ ለራሳችንና ለምንወዳቸው ወገኖቻችን ብለን መሆን አለበት” ሲሉም ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.