Fana: At a Speed of Life!

በጸረ-ሠላም ኃይሎች ጫና ውስጥ የነበሩ 289 ንጹሃን የጉሙዝ ተወላጆች ቡለን ወረዳ ማዕከል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡለን ወረዳ በዶሽና ሞች ቀበሌዎች በጸረ-ሠላም ኃይሎች ጫና ጫካ ውስጥ የነበሩ 289 ንጹሃን የጉሙዝ ተወላጆች ቡለን ከተማ ገብተዋል።

የክልልና የፌዴራል የጸጥታ አካላት በተቀናጀ መንገድ ዛሬ በጸረ-ሠላም ኃይሉ ላይ በወሰዱት እርምጃ በጫና ውስጥ የነበሩ 289 ንጹሃን የጉሙዝ የማህበረሠብ ክፍሎች ከጸረ ሠላም ኃይሎች ተነጥለው ቡለን ከተማ መግባታቸው ተገልጿል፡፡

የማህበረሠብ ክፍሎቹ ቡለን ወረዳ ማዓከል ሲገቡም አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን÷ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም መገለፁን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመተከል ዞን እየተካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር ስራ ተከትሎ ቀጠናው ወደ ነበረበት ሰላም እየተመለሰ መሆኑ ተመልክቷል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.