Fana: At a Speed of Life!

በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የትምህርት ቤት ምገባ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን 161 ሺህ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የትምህርት ቤት ምገባ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተከናወነ።

በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ የአገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይና የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ተገኝተዋል።

መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ አስተዳደር ባለፈው ዓመት በዞኑ የተማሪዎችን ምገባ ለማስጀመር ቃል በገባው መሰረት ወደ ተግባር መግባቱ ተገልጿል።

የተማሪዎች ምገባው በ669 ሚሊየን ብር የሚከናወን ሲሆን፤ 161 ሺህ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ በሚያደርገው የምገባ መርሃ ግብር ተማሪዎቹ የትምህርት ቁሳቁስና ዩኒፎርም እንደሚያገኙም ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.