Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያይቷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ዛሬ ተከናውኗል።

በሜዳው ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ወልቂጤ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሰበታ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ተገናኝተው ጨዋታውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና ከ14 ጨዋታዎች 15 ነጥብ ብቻ በመያዝ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ27 ነጥቦች ሲመራ ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ በ26 እና 25 ነጥቦች ይከተላሉ።

ወልዋሎ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ደግሞ በደረጃው ግርጌ ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.