Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሀዋሳ ከተማን አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት የመጨረሻ አንድ ጨዋታ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል።

ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ባካሄዱት በዚህ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች እንዳለ ደባልቄ በ 15ኛው፣ በ35 ኛው እና በ87ኛው ደቂቃ ላይ 3 ግቦችን ሲያስቆጥር፥ አቤል ከበደ ደግሞ  87ኛው ደቂቃ ላይ አራተኛውን ግብ አስቆጥሯል።

የሀዋሳ ከተማን የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ ብሩክ በየነ በ90ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት ጨዋታ መጠናቀቁን ተከትሎ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ10 ነጥብ ሲመራ፥ ፋሲል ከነማ፣ ባህር ዳር ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ በእኩል ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዘዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.