Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬ ዳዋ ከተማ ሲያሸንፍ አዳማና ጅማ አባ ጅፋር ወራጅ መሆናቸው ተረጋግጧል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድሬ ዳዋ ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸነፈ።

የድሬ ዳዋን ማሸነፊያ ግቦች ሪችሞንድ አይንጎ በ45ኛው እና በ90ኛው ደቂቃዎች ላይ ሲያስቆጥር ፤ ወልቂጤን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ አብዱልከሪም ወርቁ አስቆጥሯል።

ይህንን ተከትሎ ድሬዳዋ በ25 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፤ ወልቂጤ በ21 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ በወራጅ ቀጠና መቀመጥ ግድብ ብሎታል።

በሌላ በኩል አዳማ ከተማ ከ2013 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መውረዱን ማረጋገጡን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

አስር ነጥብ ብቻ የያዘው አዳማ ከተማ ቀሪዎቹን አራት ጨዋታዎች ቢያሸንፍ እንኳ ነጥቡ ሊደርስ የሚችለው 22 ብቻ በመሆኑ ነው መውረዱን ያረጋገጠው።

በተመሳሳይ ድሬዳዋ ከተማ ወልቂጤን 2ለ 1 ማሸነፉን ተከትሎ ጅማ አባ ጅፋር ከ2013 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መውረዱን አረጋግጧል።

ድሬዳዋ ከተማ በማሸነፉ ነጥቡ 25 የደረሰ ሲሆን አስረኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሲዳማ ቡና 24 ነጥብ ሰብስቧል።

ይህም 14 ነጥቦች የያዘው ጅማ አባ ጅፋር ቀሪዎቹን ሦስት ጨዋታዎች ቢያሸንፍ እንኳ ነጥቡ ሊደርስ የሚችለው 23 ብቻ ይሆናል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.